በምንጮቻችን መሰረት
ግንቦት 16 /2006 ዓ/ም በሽራሮ ከተማ ጉዕሽ ፎቶ የተባለ ሃብታም ጉቦ ለመሃንዲሶች በመስጠቱ ከመጠን በላይ ስፋት ያለው የከተማ
መሬት እንደተሰጠ ህዝብ በብኩሉ ብልሹ አሰራሩን እንዳጋለጠ ለማወቅ ተችሏል።
እንዚህ በማን
አለብኝነት ከግለሰቦች ጉቦ እየተቀበሉ የህዝብን መሬት በመስጠታቸው በህዝብ የተጋለጡ መሃንዲሶች መምህር ተክሊትና ጌታቸው የተባሉት
መሆናቸውን የገለፀው መረጃው ህዝቡ በመኖሪያ ቤቶች እጥረት ችግር ላይ ወድቆ እያለ በሽራሮ ከተማ የሚገኙ አስተዳዳሪዎችና መሃንዲሶች
ግን ከግለሰቦች ጉቦ በመብላት ያለ አግባብ ከመጠን በላይ ስፋት ያለው የከተማ መሬት ማደል የተለመደ ተግባራቸው መሆኑ ይታወቃል።