Wednesday, June 25, 2014

በትግራይ ክልል ትዳር መስርተው የሚኖሩ የሌላ ብሄር ተወላጅ የሆኑ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ከወታደር ህይወት ሲሰናበቱ በቂ የሆነ የመቋቋሚያ ገንዘብ ስለማይሰጣቸው የመሰረቱትን ትዳር ትተው ወደ ተወለዱበት አከባቢ በመጥፋት ላይ እንደሚገኙ ታወቀ፣፣



በምንጮቻችን መረጃ መሰረት አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አጋጥሞ ባለው ግርግርና ወደ ሃገራችን አሰናብቱን በሚሉ ጥያቄዎች ምክንያት የወያኔ ስርዓት ምንም አይነት መቋቋሚያ ሳይሰጥ እያባረራቸው በመሆኑ እነዚህ በመከላከያ ሰራዊት ውስጥ ሁነው በትግራይ ክልል ትዳር መስርተው የነበሩ የሌላ ብሄር ተወላጅ የሆኑ ወታደሮችም በዚህ መንገድ ኑሮአቸውን መምራት ስላልቻሉ ትዳራቸውን ትተው ወደ ትውልድ ሃገራቸው እየሄዱ መሆናቸውና መስርተውት የነበረውም ትዳር እየተበተነ መሆኑን ያገኘነው መረጃ ገለጸ።
     ይህ በእንዲህ እንዳለ እነዚህ ለአመታት ግዝያቸውን መስዋእት አድርገው ለስርዓቱ ሲያገለግሉ የቆዩ ወታደሮች የላባቸውን ዋጋ ባለማግኘታቸው የተነሳ ከበፊቱ የማይማር ከዳተኛ ስርዓት እያሉ ምሬታቸውን እየገለፁ እንደሚገኙ የተገኘው መረጃ ጨምሮ አስታውቋል፣፣