Wednesday, June 25, 2014

በሰሜን እዝ በ 11ኛ ክፍለጦር ውስጥ የሚገኙ የ6ኛ ሬጅመንት የበታች አመራሮች ሰኔ 8/2006 ዓ/ም ከነ ሙሉ ትጥቃቸው እንደጠፉ ምንጮቻችን ከቦታው ገለፁ፣፣



በመረጃው መሰረት ይህ ዓይነት እርምጃ በሁሉም እዞች እየተፈፀመ ያለ ተግባር ቢሆንም በተለይ በሰሜን እዝ የ11 ክፍለጦር የ6 ሬጅመንት አባላት በሆኑት 3 የሃምሳለቃ፤ 3 የአስር አለቃና 1መጋቢ ባሻ የሚገኙባቸው የበታች ሹማምንቶች በሰራዊቱ ውስጥ ባለው ብልሹ አሰራር ምክንያት በርካታ ወታደሮች ለ19 ዓመት ስናገለግል ቆይተናል አሁን ለተጨማሪ 7 ዓመት አንፈርምም  ወደ ቤተሰዎቻችን አሰናብቱን ብለው ላቀረቡት ጥያቄ ሰሚ ጀሮ ባለማግኘታቸው ተደራጅተው ከነ ሙሉ ትጥቃቸው ከሰራዊቱ እየጠፉ መሆናቸውን መረጃው አመለከተ፣፣
    ይህ እስከነ ሙሉ ትጥቅህ በግለሰብና በቡድን በመደራጀት እየተካሄደ ያለው ከሰራዊቱ የመጥፋት ሁኔታ በሁሉም የስርአቱ የመከላከያ እዞች እንደሆነም መረጃው አክሎ አስረድተዋል፣፣