በአማራ ክልል አብደልራፍዕ ከተማ በንግድ ስራ ላይ ተሰማርተው ኑሮአቸውን ይመሩ የነበሩ ወገኖቻችን የትጥቅ
ትግል ለሚያካሄደው የትህዴን ድርጅት መንገድ እየመራችሁ ትተባበራላችሁ በሚል ምክንያት ከአማራና ከትግራይ ክልል በመጡ የስርዓቱ
የፀጥታና የድህንነት አባልት እየተያዙ አድራሻቸው በማይታወቅበት ስፍራ ወስደው እየሰወሯቸው መሆናቸውን ከቦታው የተገኘ መረጃ አመለከተ፣፣
መረጃው በማስከተል በስርዓቱ የታጠቁ ሃይሎች እተሰወሩ ያሉ ነጋዴዎች በርካታ
መሆናቸውና ከነዚህም ውስጥ የተውሰኑትን ለመግለፅ።-
· አቶ አርአያ ሃይሉ( በወዲ ማይ-ሰሪ በሚል ቅጥያ ስም የሚታወቅ)፤
· አቶ ደጀን ተኽላይ በሽሬ ከተማ የቆየፃ አካባቢ ተወላጅ፤
· አታክልቲ ነጋና ሌሎችም ስማቸው ለግዜው ያልተዘረዘሩ
የሚገኙባቸው ሲሆኑ በስርዓቱ የፀጥታ ሓይሎች ተጠልፈው እንደተሰወሩና እስካሁንም ህላዌአቸው እንደማይታወቅ ምንጮቻችን አስታውቀዋል፣፣