Thursday, July 3, 2014

በሁመራ ከተማ የሚኖር ህዝብ ለመለስ ፋውንዴሽን የሚውል ገንዘብ ያለፍላጎቱ እንዲያዋጣ የከተማዋ አስተዳዳሪዎች እያስጨናነቁት እንደሰነበቱ ታወቀ፣፣




በምንጮቻችን መረጃ መሰረት የወያኔ ኢህአዴግ ስርዓት ካድሬዎች የተለያዩ ስሞችን እያወጡ የህዝብን ገንዘብ በማካበት የግል ኑሮአቸውን ለማመቻቸት በሁመራ ከተማ ለሚኖር ህዝባችን ሰብስበው ለመለስ ፋውንዴሽን የሚሆን ገንዘብ ክፈሉ እያሉ በማስገደድ ከአቅማቸው በላይ ገንዘብ እንዲክፍሉ እያስጨናነቋቸው እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል፣፣
     ከሁመራ ከተማ ሳንወጣ በቅርብ ቀን በከተማዋ ውስጥ ዘይት ከገባያ ጠፍቶ ከቀበሌ ለአንድ ቤተሰብ ሩብ ሊትር ተለክቶ እየተሰጠ የሰነበተ ሲሆን በአሁኑ ጊዜ ደግሞ ከቀበሌ ጠቅልሎ ስለጠፋ የከተማዋ ነዋሪ ህዝብ በገንዘቡ የሚገዛው የምግብ ዘይት አጥቶ ምሬቱን በመግለፅ ላይ እንደሚገኝ መረጃው አመልክቷል፣፣