Sunday, October 12, 2014

በሰላም አስከባሪ ስም ወደ ተለያዩ አገሮች የሚላኩ የኢህአዴግ ወታደሮች የሚሰጣቸው ደመወዝ ከ 35 እስከ 40 ፐርሰንት ብቻ እንደሆነና ቀሪውን ጀነራሎቹ እንደሚከፋፈሉት ተገለፀ፣





በምንጮቻችን መረጃ መሰረት በመላው መከላከያ ሰራዊት ውስጥ  ግምገማ ላይ በተደጋጋሚ እየተነሱ ካሉ ጥያቄዎች፤ ስርአቱ ሰላም ለማስከበር ብሎ የሚልካቸውን የሰራዊቱ አባላት፤ በመጀመርያ እነሱን ለመጥቀም እንደሆነ አስመስሎ ቢናገርም፤ ለሰራዊቱ ተብሎ ወጪ የሚደረገው ደመወዝ ግን ከ35 እስከ 40 ፐርሰንት የሚሆነውን ብቻ እንደሚሰጣቸውና፥ ቀሪውን ደመወዛቸው ግን ተቆርጦ ወደ መከላከያ ገቢ እንደሚደረግና፤ ያለ አንዳች ቁጥጥር ለጄነራሎቹ እየተሰጠ ለግል ጥቅማቸው እየዋለ መሆኑን የገለፀው መረጃው፥ ሰላም ለማስከበር የሚላከው ሰራዊት ግን ምንም አይነት ጥቅም አለማግኘቱን ለማወቅ ተችሏል፣
    ይህ በእንዲህ እያለ እየተካሄደ ባለው ስብሰባ ላይ በመከላከያ ውስጥ ባለው ሚዛናዊነት የጎደለው አሰራር ምክንያት እንዱ ተጠቃሚ ሌላኛው ተመልካች እንደሆነና፤ ሃገሪቱ ወደ ከፋ ሁኔታ እያመራች ናት የሚሉ አስተያየቶች መነሳታቸውና በስብሰባው ላይ አለመግባባቶች እንዳሉ እየቀጠሉ መሆኑን መረጃው አክሎ አስረድቷል፣