Thursday, October 2, 2014

በመቐሌ ከተማ አጋጥሞ ባለው የመብራት ሃይል እጥረት ነዋሪዎች እለታዊ ኑፘቸውን ለመምራት ተቸግረው እንዳሉ ምንጮቻችን ገለፁ።



   በመረጃው መሰረት የትግራይ ክልል ዋና ከተማ በሆነችው መቐሌ ከተማ እያጋጠመ ባለው የኤሌክትሪክ መቆራረጥ ምክንያት የግል ባለ ሃብቶችና መላው የከተማዋ ነዋሪ ህዝብ እለታዊ ስራቸውን ሊያሳልጡ እንዳልቻሉ የገለፀው መረጃው በተለይም ዳቦ ቤቶች፤ የብረታ ብረት ድርጅቶች፤ ጣውላ ቤቶች፤ ሆቴሎች፤ ካፊተርያዎችና ሌሎች በከተምዋ የተሰማሩ ዜጎች በኤሌክትሪክ መቆራረጥ ምክንያት ስራቸውን መስራት እንዳልቻሉና በውጤቱም ለከባድ ኪሳራ መዳረጋቸው ተገለፀ።
   መረጃው ጨምሮ መብራት በሌለበት ግዜ በሌሊት ወደ ሱቅና ሌሎችንም ስራዎች ለመፈፀም ሴት እህቶቻችንና እናቶቻችን በሚንቀሳቀሱበት ሰዓት የአንገታቸውን ወረቅ፤ ሞባይልና ገንዘባቸውን በሌቦች እየተቀሙ እንደሆኑና ለዚህም መፍትሄ የሚወስድ ፖሊስ ይሁን ሌላ የመንግስት አካል እንደሌለ የገለፀው መረጃው ከዚህ በፊት በውጭ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች መጥተው በነበሩበት ወቅት ለፖለቲካ ቅስቀሳና  ለማደናገር ተብሎ መብራት ያለማቛረጥ በከተማዋ ይበራ እደነበረና ከሄዱበት ማግስት ጀምሮ ግን በከተማዋ ውስጥ መብራት መቛረጡን አስመልክቶ ነዋሪው ህዝብ እየተነጋገረበት መሆኑን ተገልጸዋል።
  ይህ በንዲህ እንዳለ በከተማው ውስጥ እንደ ስኳር፤ ዘይት፤ የዳቦ ዱቄትና ሌሎች አላቂ ነገሮች ከገበያው ጠቅልለው በመጥፋታቸው ምክንያት ነዋሪዎቹ ለችግር መጋለጣቸው መረጃው አክሎ አስረድተዋል።