በመረጃው መሰረት በመቐሌ ዩንቨርስቲ የሚያስተምሩ መምህራንና ሌሎች የዩንቨርስቲው
ሰራተኞች ከእምነታቸውና ከፍላጎታቸው ውጭ ተገደው የስር አቱን ፖሊሲና እስትራተጂ ሲማሩ እንደሰነበቱ በመግለፅ ስብሰባውን እንዲከታተሉ
በማለት የስብሰባው መቆጣጠሪያ ደብተር መዘጋጀቱና በሰአቱ ተገኝቶ ላልፈረመ ተሰብሳቢም ለምን አልመጣህም አቛምህን አሳውቅ እየተባለ
ስለሚያስፈራሩት ሳይወዱ በግዴታ ለአቴንዳንስ ብለው እየተሰበሰቡ መሰንበታቸው ምንጮቻችን ገለፁ።
ከ3ቱ ካፓሶች ከአሪድ፤ ዓዲ-ሓቂና ዓይደር የመጡት በአሪድ ካምፓስ የተሰበሰቡ
ሲሆን ስብሰባው የመራውም በመቐሌ ዩንቨርስቲ የፖለቲካ ሳይንስ መምህር የሆነው የማነ ዘረአይና ሌሎች ከክልል ተልከው የመጡት የመንግስት
ባለስልጣናት መሆናቸውንና በተሰብሳቢዎች ለተነሱ ወቅታዊና ቁልፍ ጥያቄዎች አጥጋቢ መልስ ሳይሰጣቸው ሰለታለፈ ተሳታፊዎቹ እስከመቼ
ነን እያወቅን እንዳላወቅን ሁነን የምንኖረው በማለት እያማረሩ እንዳሉ መረጃው ጨምሮ ገልጿል።