ገዢው የወያኔ ኢህአደግ ስርአት አዲስ አበባ በተካሄደው ሰለማዊ ስልፍ ስለሰጋ
ህዝባዊ ሃላፊነት የማይሰማቸውን ፌደራል ፖሊሶች በማሰማራት በርከት ያሉ ንፁሃን ወገኖች እንዲታሰሩ መደረጉና ከታሰሩት መካከልም
ፍቃዱ አያሌው የቅንጅት አባል፤ ብርሃኑ መገርሳ፤ እስክንድር አብርሃምና መብርሂት አለበል የተባሉት እደሚገኙባቸው ምንጮቻችን ገለፁ።
ለነዚህ ንፁሃን ዜጎች ሊያሳስራቸው የቻለው ምክንያት ህዳር 27/2007
ዓ/ም የተካሄደው ሰለማዊ ሰልፍ በፌስ ቡክ፤ በሌሎች የመረጃ መረቦች፤ በኢሳትና ግንቦት 7 ያቀናበሩትን እናንተ የነሱ ልኡካን ሁናችሁ
ፈጽማችሁታል በሚል እደሆነ የገለጸው መረጃው ይሁን እንጅ የታሰሩት ሰዎች ከሰልፉ ውጭ እንደነበሩና ሰልፉን ያስተባቡሩትም የሰማያዊ
ፓርቲ እንጂ ኢሳትና ግንቦት 7 እንዳልሆኑ የተገኘው መረጃ ጨምሮ አስረድቷል።