በምንጮቻችን
መረጃ መሰረት የትግራይ ህዝብ በባለ-ስልጣኖቹ እየወረደበት ያለው መ’መሪያና ተከታታይ ስብሰባ በእለታዊ ስራዎቹ እንቅፋት ሁኖበት
ስላለ በአስተዳደሮች እየቀረበበት ያለውን የስብሰባ ጥሪ ባለመቀበል በስራው እየዋለ ከመሆኑ የተነሳ ለዚህ ተቃውሞ ተዋናዮች ናቸው
ያላቸውን ሰዎች ለመቆጣጠር የሚያገለግል ህግ አርቅቆ ወደ አባላቱ ለውይይት ማቅረቡ ታወቀ።
መረጃው ጨምሮ እንዳስረዳው ገዢው ጉጅሌ በምርጫ ዋዜማ እየተበባሰ በመሄድ
ላይ ያለውን የትግራይ ህዝብ ተቃውሞ ለመያዝና ለመቆጣጠር በማለት አዲስ አዋጅ በትግራይ ክልል ደርጃ እንዳረቀቁ የገለፀው መረጃው፤
የአዲሱን አዋጅ ይዘትም ማንኛውም ነዋሪ ሰው ከስብሰባ ቢቀር በገንዘብ እንዲቀጣና ለሁለተኛ ግዜ ቢደግም ደግሞ ወደ ዘብጥያ እንዲገባ
የሚያስገድድ የህዝቡን ሰብ-አዊና ዴሞክራሲያዊ መብቱን የሚያፍን አዋጅ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል።