ከመከላከያ ስታፍ አፈትልኮ የደረሰን መረጃ እንዳስረዳው በከፍተኛ የመከላከያ
ሰራዊት አመራር ውስጥ ሆኖ እየሰራ የቆየውን ሌተናል ጄነራል አበባው ታደሰ ፖለቲካዊ እንቅስቃሴህ ከኛ ጋር የለህም በሚል ምክንያት
ባለፈው ግዜ ከቦታው መባረሩና ከሱ ጋር መባረር አለባቸው ተብለው ውስጥ ለውስጥ የተጨረሰላቸው በርካታ የበላይ መኮንኖች ቢኖሩም፤
ከኋላ ሊነሳ የሚችለውን ችግር ግምት ውስጥ በማስገባት በተደረገው ግምገማ ላይ በማስጠንቀቅያ ብቻ እንዲታለፉ መደረጉን መረጃው አክሎ
አስረድቷል።
መባረር አለባቸው ተብለው ከተቀመጡት ከፍተኛ መኮነኖች አብዛኛዎቹ የሌተናል
ኮረኔል ማእረግ ያላቸው እንደሆኑ የገለፀው መረጃው የአበባው ተከታዮች ስለሆኑና እንቅፋት ስለሚፈጥሩብን ተብለው እንዲባረሩ የተወሰነባቸው
ቢሆንም፤ የኋላ ኋላ ግን በመጪው ምርጫ ላይ በህዝቡ መሃል ገብተው ኢህአዴግን ለመጣል ሊያነሳሱ ስለሚችሉ ግምገማ በማድረግ በማሰጠንቀቂያ
እንዲታለፉ መደረጋቸውን ታማኝ ምንጮቻችን በላኩልን መረጃ መሰረት ለመረዳት ተችሏል።