Sunday, December 21, 2014

በማይ-ፀብሪ ከተማ ያሉት ፖሊሶችና የፀጥታ አካላት ሃላፊዎች በቁጥጥር ስር ላይ ያሉ እስረኞችን በሌሊት በመጥራት እየገደሏቸው እንዳሉ ታወቀ።



በምጮቻችን መረጃ መሰረት በትግራይ ክልል ሰሜናዊ ምእራብ ዞን ፀለምቲ ወረዳ ማይ-ፀብሪ ከተማ በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ውስጥ በተለያዩ ምክንያቶች የታሰሩ ንፁሃን ሰዎችን የእስር ቤቱ ሃላፊዎች ከወረዳው ካድሬዎች ጋር በመመካከር በሌሊት እያስወጡ እየገደሏቸው እንዳሉ ተገለፀ።
መረጃው በመጨረሻ እንደገለፀው ይህን ዘግናኝ ተግባር የታዘበው አንድ መለስ ተዘራ የተባለ የግል ጠበቃ በእስር ቤት ውስጥ ሰዎች በፖሊሶች እየተገደሉ ያድራሉ ሲል ስለከሰሳቸው በሌሊት ወደ ቤቱ በመግባት ላይ እያለ ታህሳስ 2/ 2007 ዓ/ም እንደተገደለና ገዳዩቹም የፖሊስ አዛዦች ከካድሬዎችና ከፀጥታ ሃላፊዎች ጋር ተመሳጥረው ፈፅመውታል በማለት የከተማው ነዋሪ ህዝብ በሰፊው እየተነጋገረበት መሆኑን መረጃው ጨምሮ አስረድቷል።