Friday, December 12, 2014

በአማራ ክልል አውደራፊዕ ከተማ የሚገኙ የፌደራል ፖሊስ አባላት የተለያዩ ሴራዎችን እየፈጠሩ ነዋሪውን ህዝብ እያጋጩት መሆናቸውን ከስፍራው የደረሰን መረጃ አመለከተ።



በመረጃው መሰረት በአውደራፊዕ ከተማ የሚገኙ የፌደራል ፖሊሶች የአቶ ሃፍቱ ግርማን  የእህል መጋዝን ህዳር 22/2007 ዓ/ም በአስነሱት የእሳት ቃጠሎ 35 ኩንታል ሰሊጥና በርካታ ኲንታል ማሽላ እንደተቃጠለ ከገለፀ በኋላ ፖሊሶች ራሳቸው በፈጠሩት ወንጀል ንፁሃን ዜጎችን ጥላሸት በመቀባት ነዋሪው ህዝብ እርስ በራሱ እንዲጋጭ እያደረጉ ያልተፈለገ ግርግርና ሽብር እየፈጠሩ መሆናቸውን  ለማወቅ ተችሏል።
መረጃው ጨምሮም ይህን በፌደራል ፖሊሶች የተፈፀመ ወንጀል አንድ ስላቸው ማሙሽ ለተባለ ንፁህ ዜጋ አንተ ነህ ያቃጠልከው በማለት አስረው እያሰቃዩት እንደሚገኙ የገለፀው መረጃው የከተማዋ ነዋሪዎችም በፖሊሶች እየተፈፀመ የሚገኘውን ተግባር በመቃወም ራሳችሁ የፖሊስ አባላት  መጋዝን አቃጥላችሁ ስትሸሹ በአይናችን አይተናችኋል ስለዚህ ዜጎችን ባልዋሉበት ወንጀል እያሰራችሁ እኛንም ርስበርሳችን  አታጋጩን ሲሉ እንደመለሱላቸው ታውቋል።
 በተመሳሳይ ጥቅምት 11/ 2007 ዓ/ም የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ የፖሊስ አባላት ህዝብ እንዳይነቃባቸው ሃጎስ እምባየ የተባለ ወጣት አሻግሬ በተባለ የፖሊስ አባል ተገድሎ እያለ ሰሊጥ ሲሰርቅ ተገደለ እንዲባል በሟቹ እጂ ሰሊጥ በማስቀመጥ በተሰበሰበው ሰሊጥ መሃከል አስከሬኑን በመደበቅ በሌላ ሰው እጅ የተገደለ ለማስመሰል በአውደራፊዕ አካባቢ ነዋሪ ህዝብ ላይ ከፍተኛ ጥርጣሬ እና ግጭት እየፈጠሩ መሆናቸውን ባለፉት የዜና ስርጭታችን መዘገባችን ይታወሳል።