Wednesday, December 17, 2014

የመቐለ ከተማ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎችና ምሁራን ኢህ.አ.ዴ.ግ እየተከተለው ያለውን የካፒታሊዝም ስርዓት ድሃውን ህብረተሰብ ያማከለ አይደለም በማለት እንደተቃወሙት ምንጮቻችን ከከተማዋ በላኩት መረጃ ለማወቅ ተችሏል።



   በመረጃው መሰረት በዚህ ሳምንት በጠቅላይ ሚኒስተር አማካሪ ማዕረግ ዶ/ር ፋሲል ብሄር ብሄረሰቦችን ወክለው በመቐለ ዩኒቨርስቲ ውስጥ ተማሪዎችና ምሁራን የተሳተፉበት የፓናል ውይይት መካሄዱን የገለፀው መረጃው በፓነል ውይይቱ ላይ ተሳታፊዎች የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ስርዓት እየተከተለው ያለው የካፒታሊዝም ስርዓት ድሃውን ማህበረሰብ ያላማከለ አካሄድ ስለሆነ ለሃገራችን የሚጠቅም አይደለም በማለት እንደተቃወሙት ታውቋል።
   መረጃው ጨምሮም የፓነሉ ተሳታፊዎች በአስተያየታቸው ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ የትግሉ መነሻ አላማው ድሃውን ህብረተሰብ ያቀፈ እንደሆነ ቢናገርም ስልጣን ከተቆጣጠረ በኋላ ግን ዓላማውን ረስቶ ድሃውን ህዝብ በመካድ ሃብታሞችን ብቻ የሚጠቅም የካፒታሊዝም ስርዓት እየተከተለ ነው በማለት በስርዓቱ ላይ ያላቸውን ጥላቻ በምሬት እንደገለፁ ለማወቅ ተችሏል።