Wednesday, December 17, 2014

በትግራይ ክልል የሚገኙ መምህራን በሚከፈላቸው ወርሓዊ ደመወዝ ማህበራዊ ኑራቸውን መምራት ስላልቻሉ ስራቸውን ትተው እየወጡ መሆናቸውን ተገለፀ።



ከተለያዩ የትግራይ አከባቢዎች የደረሰን መረጃ እንደሚያመለክተው በስልጣን ላይ ያለው የወያኔ-ኢህአዴግ ጉጅሌ ባለፈው አመት የደመዎዝ ጭማሬ እንዳደረገ ብዙ ቢናገርም የተደረገው ጭማሬ ግን ከቀን ወደ ቀን እየጨመረ ያለውን የኑሮ ሁኔታ ሊቋቋም ስላልቻለ በተለያዩ ቦታዎች በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ተመድበው የሚያስተምሩ መምህራን እየተከፈላቸው ባለው ደመወዝ ኑራቸውንና የቤተሰቦቻቸውን ህይወት እየመሩ ለአመታት ሲሰሩበት ከቆዩት የስራ ዘርፍ ትተው እየወጡ እንዳሉ ታወቀ።
  መረጃው ጨምሮ እንዳስረዳው በስልጣን ላይ ያለው ገዢው የወያኔ-ኢህአዴግ ጉጅሌ የትምህርት ጥራት እያረጋገጥኩ ነኝ እያለ ባለበት ግዜ የወር ደመወዛቸው በቂ ባለመሆኑ የተነሳና በኑሮ ውድነት ምክንያት መምህራን ስራቸውን ለቀው በመውጣታቸው በትምህርት ቤቶች ላይ አጋጥሞ ያለውን የመምህራን ክፍተት ለመሙላት  ስርአቱ ችግሩን ተገንዝቦ ሊፈታው ባለመቻሉ ምክንያት ተማሪዎቹ ክፍል ውስጥ ገብተው የሚያስተምራቸው አጥተው ተቸግረው እንዳሉና በስራ ላይ አሉ የሚባሉት መምህራንም  ተመሳሳይ ስሜት ስላላቸው ለተማሪዎች አጥጋቢ እውቀት ማስተላለፍ እንዳልቻሉና የመማር ማስተማር ሂደቱም ካለፈው ግዜ በከፋ መልኩ እያስሽቆለቆለ እንዳለ ለማወቅ ተችሏል።