በምንጮቻችን
መረጃ መሰረት በንግድ ስራ ላይ ተሰማርተው በሌሎች ክልሎች የሚሰሩ የትግራይ ክልል ተወላጆች በስርዓቱ ላይ የሚታዘቡትን ብልሹ አሰራር
እየተቃወሙ ስለሚገኙ እናንተ ልትሰሩ ሳይሆን ህብረተሰቡን ልታነሳሱ ነው የምትንቀሳቀሱ ስለዚህ ወደ ክልላችሁ እናባርራችኋለን እየተባሉ
የስርዓቱ የድህነት አባላት እያስፈራሯቸው እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል።
መረጃው እንደሚያስረዳው
በተለይ ደግሞ የቀድሞ ታጋይ ለነበሩና ወታደር የሆኑትን ወገኖች ትላንት በሰራዊት ውስጥ ትረብሹን ነበር ዛሬ ደግሞ ህዝቡን ታነሳሳላችሁ
እየተባሉ በተለየ መንገድ ክትትል እየተደረገባቸው እንደሚገኝ መረጃው አመልክቷል።