Friday, December 12, 2014

ገዢው የወያኔ ኢህአደግ ስርአት እየተከተለው ያለውን አስራር የሚቃወሙ የመከላከያ ሰራዊት የበላይ አዛዦች በላያቸው ላይ ምክንያት በመፍጠር የማሰርና የማባረር እርምጃ ተጠናክሮ እየቀጠለ መሆኑን ምንጮቻችን ገለፁ።



በሰሜን እዝ የወታደራዊ ጋራዥ ሃላፊ የነበር ኮሎኔል ወዲ ስዩምና የ11ኛ ክፍለ ጦር አዛዥ የነበረው ንጉሰ ወለጨርቆስ እስር ቤት እንደሚገኙ የገለፀው መረጃው የመታሰራቸው ምክንያት ደግሞ የኢህአደግ ባለስልጣናት ለበታች የሰራዊቱ አባላት ሰብስበው ገንዘብ አጠፋፍተው ነው ያሰርናቸው ማለታቸውና ከኮሎኔል መአርግ በላይ የሆኑትን ሰብስበው ደግሞ ከተቃዋሚዎች ጋር ግንኝነት ስለነብራቸው ነው የታሰሩት ሲሉ እንደነገሯቸው ለማወቅ ተችሏል።
የደርሰን መረጃ ጨምሮ እንደገለፀው የሰራዊቱ የበላይ አዛዦች የመታሰሪያቸው እውነተኛ ምክንያት ግን የስርአቱ ባለስልጣናት እየተከተሉት ያሉትን አካሄድ ትክክል እንዳልሆነ በተለያዩ መድረኮች ሲቃወሙ በመቆየታቸው ብቻ እንደታሰሩ መረጃው አስረድቷል።
   በተመሳሳይ በከፍተኛ  የመከላከያ ሰራዊት መዋቅር ሆነው ሲመሩ ከቆዩት አንዱ የሆነው ሌተናል ጀኔራል አበባው ታደሰ አስተሳሰብህ ከኛ ጋር የለህም በሚል ምክንያት ከነበረበት የሃላፊነት ስራ ላይ እንደተባረረ ባለፈው የዜና እወጃችን መግለጻችን ይታወሳል።