የደረሰን መረጃ እንደሚያመለክተው የዞንና የወረዳ አስተዳዳሪዎች እንዲሁም
የማዕከላዊ ዞን የፖሊስ አዛዦችና የፀጥታ ሃላፊዎች ከክልል በመጡ አመራሮች ቴዎድሮስ ሓጎስ፤ በየነ መክሩና ሓዱሽ ዘነበ ህዳር
23/2007 ዓ,ም ጀምረው በስብሰባ ላይ የተጠመዱ መሆናቸውን የገለፀው ይህ መረጃ የስብሰባው አጀንዳም በህዝቡ ዘንድ ባደረጓቸው
ስብሰባዎች ላይ ስለ ምርጫ የደረሳችሁት ምን አዲስ ነገር አለ? ህዝቡ ሊመርጠን ይችላል ወይስ አይችልም? ምን ይባላል? የሚሉና
ሌሎችም መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል።
ተሰብሳቢዎች በበኩላቸው እኛ ህዝቡ መስዋእት ለከፈለው የህወሃት ድርጅት እንዲመርጥ
ብንቀሰቅሰውም አጋጥሞት ባለው የኑሮ ችግር ጥያቄዎችን ከማቅረብ ውጭ ሊሰማን አልቻለም። ስለዚህ ምርጫውን በሚመለከት አብረን ብናየው
ይሻላል በማለት የመለሱላቸው ሲሆን ስብሰባው ግን አሁንም እየቀጠለ እንደሚገኝ ምንጮቻችን የላኩልን መረጃ አክሎ አስረድቷል።