እንደ ምንጮቻችን መረጃ መሰረትበአፋርና በሶማሌ
መካከል የሚገኘውንና ቀደም ብሎ በሶማሌ ክልል ስር ሆኖው ሲተዳደሩ የነበሩትን ገዳማዊት፤ ዕንድሮና ዓዳይቲ የተባሉት የኢሳ ጎሳዎች
ሲኖሩበት የቆዩት 3ቱ ከተሞች በአፋርና በኢሳ መሃል በርካታ ግጭት ሲካሄዱባቸው እንደነበር የተሚታወቅ መሆኑንና
የተፈፀመው ድርጊት የኢህአዴግ ስርአት በአፋር ክልል ህዝብ ያጣውን ተቀባይነት ለማግኘት ሲል ከተሞቹ ወደ አፋር ክልል እንዲጠቃለሉ
ማድረጉ በሶማሌ ህዝብ ተቀባይነት እንዳላገኘ የተገኘው መረጃ አስታወቀ።
ለአፋር ክልል
አስተዳደር ተላልፎ የተሰጠውን መሬት የሰማል ክልል ፕረዚደንት እንዳልተቀበለውና
በውሳኔው ላይ ቅሬታ እንደነበረው በርክክቡ ወቅት የነበሩ ወገኖች መናገራቸውንና የሶማሌ የሃገር ሽማግሌዎችና የሃይማኖት መሪዎችም
ቢሆኑ ውሳኔውን ሳያምኑበት ስላልተቀብሉት በኢህአዴግ ባለ-ስልጣናት ሃይል በርክክቡ ወቅት እንዲገኙ ቢደረጉም የተወሰደውን ውሳኔ
ፍትሃዊነት የጎደለው በመሆኑ በባሰ መንገድ ወደ ደም ማፋሰስ የሚያመራ ነው በማለት ወደ ፌደራል ሄደው ብሶታቸውን እንዳቀረቡ ለማወቅ
ተችሏል።