Wednesday, December 17, 2014

ከሳውዲ አረቢያ የተመለሱ ወገኖቻችን በስርዓቱ የተገባላቸው ቃል በተግባር ስላልዋለ ዳግመኛ ወደ ስደት እየጠፉ መሆናቸው ተገለፀ።



የደረሰን መረጃ እንደሚያስረዳው በሳውዲ አረብያ በስደት ሲኖሩ የነበሩና በስልጣን ላይ ባለው የወያኔ ኢህአዴግ ስርዓት የሚያስፈልገው ሁሉ እንደሚሟላቸውና በየጊዜው ሁኔታዎች እየታዩ እገዛ እንደሚደረግላቸው ቃል ተገብቶላቸው ወደ ትውልድ ሃገራቸው የተመለሱ ዜጎቻችን ስርዓቱ የገባላቸውን ቃል ሙሉ በሙሉ ስለተካዱ  ህይወታቸውን ለመምራት ሲሉ ዳግመኛ በበረሃና በባህር እያቋረጡ ወደ ማያዉቁት ሃገር እየጠፉ መሆናቸውን ምንጮቻችን አስታውቁ።
   በስልጣን ላይ ያለው ስርዓት ባሳለፍነው ዓመት እንደ ትልቅ አጀንዳ ብዙ ቢናገርበትም ለዜጎቹ ጠበቃ መስሎ የቀረበበት ምክንያትም የማያውቀውን የዓለም ህዝብ ለማደናገር ያደረገው እንጂ እነዚህ ከሳውዲ-አረብያ ከተመለሱ በኋላ ይሰጣቸዋል የተባለው የመቋቋሚያ ገንዘብ ቀርቶ ከባንክ ገንዘብ ውሰዱና ሰርታችሁ ትመልሳላችሁ ስለተባሉ ከስደት ተመላሾቹ በበኩላቸው ብድር በሚጠይቁበት ሰዓት ዋስ አቅርቡ፤ የሚያዝ ንብረት አምጡ፤ ከናተ በፊት የሚሰጡ አሉን በሚሉ አሰልቺ ነገሮች ስቃይ ስለበዛባቸው ዳግመኛ ወደ ስደት እያመሩ መሆናቸውን ለችግሩ ሰለባ የሆኑ ቤተሰቦቻቸውን መሰረት በማድረግ የደረሰን መረጃ አመለከተ።
   ቤተሰቦቻቸው እንዳያግዟቸው በድህነት ውስጥ ስለሚገኙ የሚወዷቸው  ልጆቻቸውና ወንድም እህቶቻቸው እየጠፉ በሚሄዱበት ሰዓት ዝም ብለው እንዲያዩዋቸው ተገደው እንደሚገኙ የገለፀው መረጃው። በተለይ በአፅቢ ወንበርታና አካባቢው በ4 ወር ብቻ ከአንድ ቀበሌ ከ100 ወጣቶች በላይ ወደ ስደት እንዳመሩ ለማወቅ ተችሏል።