ምንጮቻችን እንደገለፁት በተለያዩ የትግራይ ዞኖችና ወረዳዎች የሚገኙ የህወሃት
ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ አስተዳዳሪዎች ጥር 16 ቀን 2007 ዓም በመጪው ምርጫ ጉዳይ ላይ ባስተላለፉት የምርጫ ቅስቀሳ ወቅት ይህ ወጣት
እያጋጠመው ያለውን ማህበራዊ ችግር አስመልክቶ እየተቃወመ መሆኑን ከገለፀ በኋላ “ዛሬ ብቻ ካርድ አውጥታችሁ ምረጡን እንጂ በኢ.ህ.አ.ዴ.ግ የሚመራው መንግስታችን ሁሉንም ችግራችሁን
ይፈታላችኋል” በማለት እየተመፃደቁ መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል።
ሆኖም ግን በእነዚህ አስመሳይ ቅስቀሳ በሚያካሂዱ
የገዥው መንግስት ድርጅት የተሰላቸው ወጣት “ህወሃት በማይተገበሩ ቃልኪዳኖች ወላጆቻችንን አስገብቶ እኛንም እንዲያስገባን አንፈቅድም”
በማለት ዛሬ ይሁን ነገ ከእናንተ የምንጠብቀው ለውጥ ስለሌለ የፖለቲካችሁ መሳሪያ አንሆንም የምንመርጠው ድርጅትም ስለሌለ የምርጫ
ካርድ አንወስድም በሚል ተቃውሞ ላይ እንደሚገኙ ጨምሮ አስረድቷል።