በምንጮቻችን መረጃ መሰረት በዞኖችና በወረዳዎች
በስርዓቱ ተሹመው ሲያገለግሉ የቆዩ ዜጎች ለስርዓቱ ታማኞች አይደላችሁም ችግር አለባችሁ እያሉ ከነበራቸው ሃላፊነት አባረዋቸው ሲያበቁ
ዛሬ በስልጣን ባለው የኢህአዴግ መንግስት ላይ የተቃውሞ ቅስቀሳ እያደረጉ
ህዝቡን ከጎናቸው በማሰለፋቸው የተደናገጡት እነዚህ ባለስልጣኖች ፀረ መንግስታችን ቅስቀሳ አታድርጉ እንጂ ገንዘብም ይሁን ስልጣን
እንሰጣችኋለን በማለት የሃገር ሽማግሌዎችን በመያዝ ታረቁን እያሏቸው እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል።
ከስልጣናቸው ተባረው የቆዩና አሁን በህወሃት
እየተለመኑ ካሉ ሰዎች እንደአብነት ለመጥቀስ- በበርሃለ ወረዳ የውሃና ማዕድን ሓላፊ የነበረ ግለሰብ ከዚህ በፊት ችግር አለብህ
ተብሎ ከስልጣኑ ተባሮ የነበረ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት ማንም ሰው ለኢህአዴግ መምረጥ እንደሌለበት በመቀስቀስ በርካታ ህብረተሰብ ከጎኑ
በማሰለፉ ስጋት ውስጥ የገቡት የስርዓቱ ባለስልጣናት ጥር 20/2007 ዓ.ም የክልሉ የፀጥታ ሃላፊ ስዩም አወል የተባለ ባለስልጣን
በሽማግሌዎች በኩል አድርጎ 30 ሽህ ብር እንደሚሰጥውና ወደ ነበረበት የስራ ሓላፊነትም ፍቃደኛ ከሆነ መመለስ እንደሚችል እንደነገረው
ለማወቅ ተችሏል።