Thursday, February 5, 2015

በአነስተኛና ጥቃቅን ተቋማት ስራ ተሰማርተው የሚሰሩ ወጣቶች ገና ሳይጀምሩ ከአቅማቸው በላይ ግብር እንዲከፍሉ በመገደዳቸው ምክንያት ተቋማቸውን ዘግተው እየጠፉ መሆናቸውን ምንጮቻችን አስታወቁ።



በትግራይ ክልል በተለያዩ ከተሞች የሚገኙ ወጣቶች በማህበርና በግል በመሆን በጥቃቅንና አነስተኛ ስራዎች ተሰማርተው መንቀሳቀስ በጀመሩበት ሰዓት ገና የተበደሩትን ገንዘብ ሳይመልሱ ከገቢያቸው ጋር የማይመጣጠን ግብር ክፈሉ እየተባሉ መሆናቸውን የገለፀው ይህ መረጃ በተለይ ደግሞ ምግብ-ቤትና የመሳሰሉ ተቋማትን ከፍተው ለሚሰሩ ወጣቶች የግብር አወሳሰኑ የተጋነነ ከመሆኑ የተነሳ እኛ ክፈሉ የምትሉንን ግብር መክፈል አንችልም በማለት ተቋማቸውን ዘግተው እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል።
  መረጃው አክሎ እንደሚያስረዳው እነዚህ የንግድ ስራ የጀመሩ ወጣቶች ክፈሉት እየተባሉት ያለው ግብር ካላቸው ገቢ ጋር ስለማይመጣጠን አስተያየት እንዲደርግላቸው ለሚመለከታቸው አካላት ጥያቄ ቢያቀርቡም የሚሰማቸው ስላጡ የሚያበረታታ መንግስት ያለ መስሎን ነው እንጂ ሰርተን ያገኘነውን ገቢ ኑሮአችንን ማሻሻል ስንችል ጠቅልላችሁ አስረክቡን የምንባል ከሆነስ የንግድ ፍቃዳችሁን ተረከቡን እያሉ ወደ ስደት በማምራት ላይ እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል።