ከወረዳው የፖሊስ ፅህፈት ቤት ሾልኮ የደረሰን መረጃ እንደሚያመለክተው
እነዚ የመሰናበቻ ጥያቄ አቅርበው ያሉ የፖሊስ አባላት በስልጣን ላለው ስርዓት ለረዥም ጊዜ እያገለገልን መጥተናል ቢሆንም ግን እየተከፈለን
ባለው ደመወዝ ማህበራዊ ህወታችንን ለመምራት ስለተቸገርን የጡረታ መብታችን ተከብሮ የመሰናበቻ ወረቀት ይሰጠን በማለት ጥር 12
/2007 ዓ.ም ወደ ወረዳው አቤቱታቸውን እንዳቀረቡ ለማወቅ ተችሏል።
የመሰናበቻ ጥያቄ ካቀረቡ የፖሊስ አባላት የተወሰኑትን ለመጥቀስ ያህል
ረዳት ኢንስፔክተር ሽመንዲ፤ ረዳት ኢንስፔክተር ሱራፊኤል፤ ረዳት ኢንስፔክተር ገብረዋህድ፤ ረዳት ኢንስፔክተር በርሀ ከአዲ-ሃገራይ
አካባቢ፤ ረዳት ኢንስፔክተር አሸብር ገብረመድህና ሌሎችም የሚገኙባቸው በተደጋጋሚ ጥያቄ እያቀረቡ የቆዩ ሲሆን አሁንም የነበረውን
አቤቱታቸውን አጠናክረው እየቀጠሉበት እንደሚገኙ የደረሰን መረጃ አክሎ አስታውቋል።
እነዚህ የመሰናበቻ ጥያቄ እያቀረቡ የሚገኙት የፖሊስ አባላት ከ22 አመታት
በላይ ሲያገለግሉ የቆዩ ሲሆን በስልጣን ያለው ስርዓት ለነዚህ ሰዎች ከአገልግሎታቸው ጋር የሚመጣጠንና ጥቅም ሊያገኙበት የሚችሉበትን
መንገድ ማመቻቸት ሲገባው አድልዎ እየፈፀመባቸው ተጠቃሚዎች ሊሆኑ ስላልቻሉ ለስልጣን ማራዘሚያ ልንሆን አይገባም በማለት እየወሰዱት
ያለ አማራጭ እንደሆነ መረጃው በመጨረሻ አስታውቋል።