በምንጮቻችን መረጃ መሰረት።- የመቐለ ከተማ
ነዋሪ ህዝብ በአጠቃላይ በአስተዳደራዊ ችግር እየተሰቃየ መሆኑን የገለፀው መረጃው። በተለይ በሃወልቲ ክፍለ ከተማ አካባቢ አስተዳደር
ልዩ ስሙ ደብሪ የሚገኝ ህዝብ ባለፈው ክረምት በተከታታይ የትራንስፎርመር ብልሽት ሲከሰት በመቆየቱ የተነሳ። ይህንን
ለመተካት አስተዳደሩ ከመከላከያ ኢንጂነሪንግ ትራንስፎርመር በማስመጣት ዘላቂ መፍትሔ እናደርጋለን ወዘት በማለት ከ7 ወር በላይ
ተጠብቆ ምንም ለውጥ ሊያመጣ እንዳልቻለ ለማወቅ ተችሏል፣
በተጨማሪም
በአስተዳደሩ የሚታየው አድርግልኝ ላድርግልህ የወለደው ፀረ ዲሞክራሲያዊ አሰራር በሁሉም የከተማዋ ጽሕፈት ቤቶች ተስፋፍቶ
አገልግሎት የሚፈልገውን ማህበረሰብ ባንድ መስሪያቤት ሊጨረስ የሚገባውን ቀላል ነገር የሚሰማው አካል እያጣ ካንዱ ወደ አንዱ እየተሸጋገረ
ቀናትን የሚፈጅ በመሆኑ ነዋሪው ህዝብ በአስተዳደሩ ላይ ያለውን ምሬት እየገለፀ መሆኑ ታውቋል፣