በዞኑ በእርሻ
ስራ ተሰማርተው በመስራት ላይ ያሉት ኢንቨስተሮች በውል የማያውቁት የመሬት ክራይ በገዢው የኢህአደግ አስተዳዳሪዎች ትእዛዝ እንደተሰጣቸው
የገለፀው መረጃው። ኢንቨስተሮቹ ህጋዊ የመንግስት ግብር እየከፈሉ ቢቆዩም። አሁን ክፈሉ እየተባሉት ያሉት የመሬት ክራይ ግን በውል የማያውቁትና አዲስ ሃሳብ መሆኑና። ይህ ድርጊትም ሆን ተብሎ ገንዘባቸውን
ለመቀማት የተሸረበ ሴራ መሆኑን ባለ ሃብቶቹ በምሬት እየገለጹ መሆናቸውን
ለማወቅ ተችሏል፣
በተለይ በቃፍታ ሑመራ። ማይ ካድራ አካባቢ ተሰማርተው የሚገኙት ከ12
በላይ ኢንቨስተሮች። በካድሬዎቹ ተገደው እንዲከፍሉ የታዘዙትን የገንዘብ መጠን ክፈሉ በተባሉበት ጊዜ። በገበያ ላይ የሰሊጥ ዋጋ
በማሽቆልቆሉ ምክንያት። ብዙ ወጪ አድርገን ያፈራነው ምርት በተፈለገው ዋጋ መሸጥ ስላልቻልን አሁን መክፈል አንችልም ስላሉ ብቻ
ክስ እንደተመሰረተባቸው መረጃው አስረድቷል፣
ከተከሰሱት 12 ኢንቨስተሮች መካከል። ነጋ ባንቴ የ121 ሄክታር የእርሻ መሬት
120ሺ ብር፤ አለም ገብረፃዲቅ የ30 ሄክታር መሬት 30ሺ ብር እንዲከፍሉ የተወሰነባቸውና ሌሎችም በተመሳሳይ ከህግ ውጭ የመሬት
ክራይ በሚል ሰበብ ገንዘብ እንዲከፍሉ እየተገደዱ መሆናቸው መረጃው አክሎ አስረድቷል፣