በዞኑ ውስጥ አምቦ ወረዳ፤ ብሎ ቀበሌ የሚገኙ የመድረክ ተቃዋሚ ድርጅት አባላት። ድርጅታዊ
ስራቸውን እንዳይሰሩ በስርአቱ ተላላኪ ካድሬዎች እንቅፋት እየደረሰባቸው መሆኑንን የገለጸው መረጃው። ግፍ እየደረሰባቸው ከሚገኙትም
የመድረኽ ተቃዋሚ ድርጅት የህዝብ ግንኝነት ኃላፊ የሆነው አቶ ተካ
ቢነጋ የተባለው ወገን። ባለፈው መጋቢት ወር የድርጅቱን በራሪ ወረቀት ወደ ተለያዩ ቀበሌዎች ይዞ በሚሄድበት ጊዜ። የስርአቱ ተላላኪ
ካድሬዎች በረሃ ላይ በመጠበቅ። የያዘውን ወረቀት ነጥቀው ደብድበው እንዳባረሩት የተገኘው መረጃ አስታወቀ፣
መረጃው በማስከተል። በመጪው ግንቦት ወር ላይ ከሚካሄደው አስመሳይ ምርጫ
ጋር ተያይዞ። በወረዳው ውስጥ በተቃዋሚ ድርጅቶች የሚካሄደውን እንቅስቃሴ ለማሰናከል። ካሁኑ ጀምሮ በአካባቢው በርካታ የፌደራል
ፖሊሶች ተሰማርተው እንደሚገኙ መረጃው አክሎ አስረድቷል፣