በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፤ ከንባታ ዞን ዱራሜ
ከተማ ውስጥ የሚኖረው ህዝብ በመሰረተ ልማት እጦት ምክንያት ማህበራዊ ህይወቱን ለመምራት ተቸግሮ እንደሚገኝ የገለፀው መረጃው። የአካባቢው ህብረተሰብ ያፈራውን የእርሻ
ምርት በወቅቱ ወደ ጅማ ሄዶ እንዳይሸጥ ከዱራሜ ወደ ጅማ የሚያሻግረው የኦሞ ወንዝ ድልድይ ስላልተሰራለት ህዝቡ እለታዊ ኑሮውን
እንዳይመራ እንቅፋት ሁኖበት እንደሚገኝ። ነዋሪዎችን መሰረት በማድረግ የተገኘው መረጃ አስታወቀ፣
ነዋሪዎቹ በማስከተል። በተለይ! ጊዜ የማይሰጡ ፍራፍሬዎችና አትክልቶች።
በአካባቢው የመንገድ ትራንስፖርት ግንባታ እጥረት ምክንያት። ለኪሳራ እየተጋለጡ መሆናቸውንና። ይህ ችግር በወቅቱ መፍትሄ ካልተደረገበትም
ለከፋ ኪሳራ እንደሚጋለጡና በተለይ በክረምት ወራት በደቡብ ህዝብና በኦሮሚያ የሚደረገው የንግድ ልውውጥ ጠቅልሎ እንደሚቋረጥ አስተዳደሩ
የሚያውቅ ቢሆንም። እስካሁን ግን ምንም አይነት መፍትሄ ማበጀት እንዳልተቻለ
ለማወቅ ተችሏል፣