Thursday, May 21, 2015

አገራችንና ህዝባችን ማዳን አላማ አድርገን በአንድነት እንሰራለን በሚል መሪ ቃል ትህዴንን ጨምሮ አምስት የትጥቅ ትግል የሚያካሂዱ የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ድርጅቶች እየተወያዩ መሆናቸው ተገለፀ።



    የአንድነት፤ መከባበር፤ መቻቻልና የነፃነት ተምሳሌት የሆነችውን አገራችን ኢትዮጵያ ፀረ ህዝብ አላማቸውን ለማሳካትና የስልጣን እድሜያቸው ለማራዘም ላይና ታች እየተወራጩ የሚገኙትን የህወሃት/ኢህአዴግ ቡድን አገሪቱና ህዝቡን ከመቼውም ግዜ በላይ በከፋ ደረጃ ላይ ማድረሳቸውን አምስቱ ተቃዋሚ ድርጅቶች መግለፃቸው የተገኘው መረጃ አስታወቀ።
    አገሪቱና ህዝቡ በእንደዚህ አይነት የከፋ ሁኔታ መቀጠል የለበትም፤ የህወሃት/ኢህአዴግ የግፍ አገዛዝ ሊበቃው ይገባል በሚል ቀደም ብለው ስርአቱን በትጥቅ ትግል እየታገሉት የሚገኙት ድርጅቶቹ ህዝቡን ወደ አንድ አስተሳሰብ በማምጣት አገሪቷ ነጻ የምትወጣበት ግዜው አሁን መሆኑንና በስልጣን ላይ ያለውን ስርዓት ለማስወገድ በሚደረገው ትግል ላይ ተባብረን መስራት ይጠበቅብናል በሚል ውይይት ላይ መሆናቸውን የተገኘው መረጃ ለማወቅ ትችሏል።
    ስልጣን ላይ የሚገኘውን የህወሃት ኢህአዴግ ቡድን ለማስወገድ  በትብብር፤ በጥምረትና ብሎም በውህደት ለመስራት የሚያስችላቸው ሁኔታ ላይ እየተወያዩ ያሉት ድርጅቶች
1, የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ
2, የጋንቤላ ህዝብ ነፃነት ንቅናቄ
3, የቤንሻንጉል ህዝብ ነፃነት ንቅናቄ  
4, የአማራ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ሃይሎች ንቅናቄ
5, የአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ንቅናቄ ሲሆኑ ከሁሉም በፊት አገራችንና ህዝቡን ማዳን ቀዳሚ ግባቸን አድርገን እንሰራለን የሚል መሪ ቃል በማስቀመጥ በሁሉም እንቅስቃሴዎች ተባብረው ለመስራት የሚያስችል ውይይት እያካሄዱ መሆናቸውን ለመላው ያገራችን ህዝብ መልእክት አስተላልፈዋል።
      አምባገነኑ የህወሃት/ ኢህአዴግ ስርዓት ልክ እንዳለፉው  የይስሙላ ምርጫ ለማካሄድ ደፋ ቀና እያለ ይገኛል፣ እናም መላው ያገራችን ህዝብ ስርዓቱን በመቃወም አስፈላጊውን እንቅስቃሴ እንዲያደርግና በተደራጀ መልክ እየተንቀሳቀሱ ከሚገኙ ተቃዋሚ ድርጅቶች ጋር በመሆን ድርሻውን መወጣት እንዳለበት ውይይት ላይ የሚገኙ ተቃዋሚዎች መልእክት ማስተላለፋቸውን የተገኘው መረጃ አክሎ አስረድቷል።