አቶ ደመቀ መኮነን በሚወዳደርበት ደብረማርቆስ አካባቢ ግንቦት
3/2007 ዓ/ም የምረጡኝ ቅስቀሳ ማካሄዱን የገለፀው መረጃው በየአምስት
ዓመቱ መጥተህ ምረጡኝ ከማለት በስተቀር ለህዝቡ የጠቀምከው ነገር የለም በምርጫ ወቅት ምረጡኝ ከማለት በስተቀር በክልሉ ይሁን አጠቃላይ
በሃገር ደረጃ ያመጣሀው ለውጥ የለም ስለዚህ ለውጥ ማምጣት ለሚችል ድርጅት ነው የምንመርጠው ብለው እንደተናገሩት የተገኘው መረጃ
አስረድቷል።
ህዝቡ ጨምሮ እንተ በህዝቡ ገንዘብ ኑሮህ ስለተለወጠ እኛ አልፎልናል ማለት
አይደለም፣ ስለዚ የጎጃምን ህዝብ ምረጡኝ እያልክ አታስጨንቀው በአካባብያችን ምንም ዓይነት የመሰረተ ልማት ለውጥ ልታመጣ አልቻልክም
እናም አንተን የምንመርጥበት ምክንያት የለም በማለት ሃሳቡን መቃወማቸውንና በተቃውሞ መልክ ሃሳባቸውን ከገለፁ ሰዎች መካከልም አቶ
ስመኘው ክብረቱ የተባለ ወገን እንደሚገኝበት መረጃው አክሎ አስረድቷል።