Sunday, May 17, 2015

በደብረ ማርቆስ ከተማ የመኪና መንጃ ፈቃድ ለማውጣት በግል ማሰልጠኛ ማዕከሎች ሲሰለጥኑ የቆዩ ብቁ ዜጎች ለፈተና መግቢያ ጉቦ እየተጠየቁ መሆናቸውን ከስፍራው የደረሰን መረጃ አመልክቷል።



    በደብረ ማርቆስ ከተማ በሚገኙ የግል የተሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ ማዕከሎች ለበርካታ አመታት ሲሰለጥኑ የቆዩ ተማሪዎች ስልጠናውን ጨርሰው ከመንግስት የብቃት ወረቀት እንዲሰጣቸው በሚጠይቁበት ጊዜ የገዥው መንግስት ተላላኪ ካድሬዎች ከትራፊክ ፖሊስች ጋር በመሆን ለፈተና በሚቀረፀው የተሽከርካሪዎች ቪዲዮ ትክክለኛና ህጉን እየተከተለ እያለ አመራሮች ግን ምንም ዓይነት ስህተት የሌለባቸውን የተማሪዎች የብቃት ወረቀት እንዲሰጣችሁ ከፈለጋችሁ  በነፍስወከፍ ከ2 ሺህ ብር በላይ መክፈል አለባችሁ የሚል መልዕክት በስውር እንደተላከላቸው ለማወቅ ተችሏል።
    ይህንን ተከትሎም ምንም ዓይነት ብቃት የሌላቸው የሃብታም ልጆች ከተጠየቀው የጉቦ መጠን በላይ በመክፈል የመንጃ ፈቃድ ሲያወጡ ብቃት ያላቸው የድሃ ልጆች ግን ለጉቦ የሚሆን ገንዘብ ማግኘት ባለመቻላቸው እስካሁን የብቃት ወረቀቱ ሊሰጣቸው እንዳልቻለ ከስፍራው የሚገኙ ምንጮቻችን ዘግበዋል።