ምንጮቻችን ከከተማዋ እንደገለፁት በኦሮሚያ ክልል ወሊሶ ከተማ የሚገኙ
አርሶ አደር ወገኖቻችን የካድሬዎች መሬት ተገደው እንዲያርሱት መደረጉን የገለጸው መረጃው አቶ ሲሳይ ከልካይ የተባለ የስርዓቱ የፖሊስ
አባል ሰኔ 29/ 2007ዓ/ም አቶ ጫላ ፈይሳ ለተባለ አርሶ አደር መሬቴን ለምን አላረስክልኝም በማለት ስለ አፋጠጠበት አርሶ አደሩም
በኔ ጉልበት ልትጠቀም ልታስፈራራኝ አይገባህም ስላለው ብቻ ፖሊሱ ጥይት ተኩሶ እጁን ስለአቆሰለው አቶ ጫላ ፈይሳ በከባድ ቆስሎ
ወሊሶ ሆስፒታል ተኝቶ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል።
መረጃው ጨምሮ እንዳስረዳው-ይህ የስርአቱ ካድሬዎች የግፍ ተግባር በወሊሶ ከተማ
ብቻ የታየ ሳይሆን በሁሉም የሃገራችን አካባቢዎች እየታየ ያለና የነበረ መሆኑን መረጃው ጨምሮ አስረድቷል።