Saturday, July 18, 2015

የመቐለ ከተማ ነዋሪ በአላቂ ነገሮች እጥረት እጅግ በመቸገሩ ምክንያት ምሬቱን እያሰማ መሆኑን የደረሰን መረጃ አመለከተ።



   ምንጮቻችን ከመቐለ ከተማ እንዳስታወቁት የመቐለ ከተማ ነዋሪ ህዝብ በአላቂ ነግሮች እጥረት ምክንያት እየተሰቃየ መሆኑን የገለጸው መረጃው በተለይም ከሰኔ 12 2007ዓ/ም ጀምሮ እንደ ዘይትና በርበሬ የመሳሰሉት ጠቅልለው ከገበያ ስለጠፉ በዚህ ሳቢያም አንዳንድ ነጋዴዎች ለአንድ ኪሎ በርበሬ ከ160 ብር እስከ 180 ብር እየሸጡት መሆኑና በዚህ ሳብያም ነዋሪዎች ስራቸውን ትተው አላቂ ነገሮችን ለማግኘት ሲሉ በየ ሱቆች እየተንከራተቱ መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል።
    መረጃው ጨምሮ በዚህ የተማረረ ህዝብም በብዱን በመሆን የመቐለን ከተማ የጅንአድ ሃለፊ ወደሆነው ባለስልጣን በመሄድ ለምንድ ነው? በአላቂ ነገሮች እጥረት ህዝቡን እየተቸገረ ያለው በማለት አቤቱታቸው በገልፁበት ጊዜ በመርከብ እየመጣ ስለሆነ ትንሽ ጠብቁን የሚል ምላሽ በመስጠት እንደቀለደባቸው ለማወቅ ተችሏል።