Friday, August 7, 2015

በትግራይ ክልል የሚገኙ በስፖርት ፌደረሽን ውስጥ ተመድበው እየሰሩ የቆዩት አመራሮች ከብልሹ አሰራር በተያያዘ ከባድ ንትርክ ውስጥ መግባታቸውን ከመቐለ ከተማ የደረሰን መረጃ አስታወቀ።



    የትግራይ ክልል የስፖርት ፌደረሽን ባለስልጣኞች በከፋ ግጭት ውስጥ መግባታቸውና አንደኛ ቡድን እየተባለ የሚጠራው  የስፖርት ፌደረሽኑ መሪ ምክትል ኮምሽነር ቴድሮስና የሁለተኛው ቡድን መሪ አማኑኤል የተባለው ባለስልጣን እንደሆኑ የገለፀው መረጃው ሁለተኛ ቡድን ላይ የሚገኙት ለስፖርት ተብሎ የተመደበውን በጀት በአንደኛው ቡድን እየተጠፋፋ ነው በሚል መወነጃጀል ውስጥ ገብተው እየተካሰሱ መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል።
    አማኑኤል በተባለው ባለስልጣን የሚመራው የሁለተኛው ቡድን በድብቅ ጉባኤ በማካሄዳቸው ምክንያት አንደኛ ቡድን ላይ የሚገኙትን  ለምን እኛ ሳናውቅ በድብቅ ጉባኤ አካሄዳችሁ በሚል ግጭት ውስጥ መግባታቸውና ይህንን የታዘበው ህብረተሰቡም የትግራይ ስፖርት እድገት እንዳያሳይ እያደናቀፋችሁ ነው በማለት ምሬታቸውን በመግለፅ ላይ መሆናቸውን የተገኘው መረጃ ጨምሮ አስረድቷ።