Friday, August 7, 2015

በፀገዴ ወረዳ፤ ግጨው በተባለው አካባቢ የትግራይና የአማራ ክልል አርሶ አደሮች በከፍተኛ ውጥረት ላይ መሆናቸውን ከአካባቢው የተገኘው መረጃ አስታወቀ።



    ይህ በክልል አንድና ክልል ሦስት መሃከል የሚገኘው የእርሻ መሬትን ምክንያትን ያደረገ ሃምሌ 15/ 2007 ዓ/ም የተነሳው ብጥብጥ ሁኔታውን የሚያረጋጉት መስለው ነገሩን በማባባስ ላይ ተሰማርተው የሚገኙት የሁለቱም ክልል ሚሊሻዎች ራስ በራሳቸው ተጋጭተው በለኮሱት የተኩስ ልውውጥ ከአርማጭሆ የመጡ ሁለት ሚሊሻዎች እንደተገደሉ ለማወቅ ተችሏል።
    በተደረገው የተኩስ ልውውጥ ህይወታቸው ያለፉ ግርማይና በላይነህ የተባሉ ግለሰቦች ሲሆኑ ከግዜ ወደ ግዜ እየተባባሰ ያለውን የሁለቱ ህዝቦች ግጭት የሚፈታ አካል ባለመገኘቱ በአካባቢው የሚኖሩ የትግራይ ተወላጅ አርሶ-አደሮች የክረምት አዝመራውን እስካሁን መጠቀም ባለመቻላቸው በከባድ የማህበራዊ ቀውስ ላይ ወድቀው እንደሚገኙ መረጃው አክሎ አስረድቷል።