በምዕራብ ትግራይ ዞን በረኸት አካባቢ በምትገኘው ግዲማ በተባለው አካባቢ
ሃምሌ 9ቀን 2007 ዓ/ም የሱዳን ሰራዊት ድንበር ተሻግሮ ወደ ኢትዮጵያ መሬት መግባቱን የገለፁት ምንጮቻችን ይህንን ተከትሎም
የአካባቢው ነዋሪ የሆኑት ወገኖቻችን ከመኖሪያ ቤታቸው እንዲፈናቀሉ እየተገደዱ ሲሆን የለቀቁትን ቦታ ደግሞ ሱዳናዊያን ሃብታሞች
ስላረሱት ከስፍራው የተፈናቀሉ ዜጎች ወደ ኢትዮጵያ መንግስት ጥሪያቸውን በማሰማት ላይ መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል።
መረጃው ጨምሮም በተጠቀሰው እለት የኢትዮጵያ መከለከያ ሰራዊትና የፌድራል
ፖሊስ ወደ ቦታው በመሄድ ሙሉ ቀን የፈጀ ከሱዳን መከላከያ ሰራዊት ጋር ከባድ ውጊያ ሲያደርጉ የዋሉ ሲሆን ከሁለቱም ወገኖች የሞቱትና
የቆሰለቱን በተመለከተ እስካሁን የወጣ መረጃ እንደለለ አስረድቷል።
ከተካሄደው ውጊያ በኋላ የኢትዮጵያ ሰራዊት ወደ ኋላ ተመለስ ተብሎ ስለተመለሰ
የእርሻ መሬታቸንና የሃገራችን መሬት እየተወረረ እያለ ለምን መንግስት ተመለሱ ይላል ቀጣይ የሆነ እርምጃስ ለምን አይወስድም በማለት
በስርዓቱ ላይ ከፍተኛ የተቃውሞ ድምፅ እየተሰማ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።