Sunday, August 2, 2015

በትግራይ ደቡባዊ ዞን፤ አላማጣ ከተማ ውስጥ፣ አንድ የትራፊክ ፖሊስ አባል ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች ሓምሌ 3/2007 ዓ/ም ላይ በስለት ተወግቶ መገደሉን ምንጮቻችን ከቦታው ገለፁ።



    እንደ ምንጮቻችን መረጃ መሰረት፣- ነዋሪነቱ በትግራይ ደቡባዊ ዞን፤ በአላማጣ ከተማ የፖሊስ ትራፊክ አባል የሆነውና በአላማጣ መኾኒ መስመር ላይ የሚሰራው ቢያርግልኝ ውቤ ሸምሱ የተባለው ግለሰብ፣ በተደጋጋሚ በአላማጣና አካባቢው ህዝብ ጉቦ ይቀበላል እየተባለ ሂስ እየተሰጠው የነበረ እንደሆነ የገለጸው መረጃው፣ ከዚህ አፀያፊ ተግባሩ መቆጠብ ስላልቻለ፣ ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች መገደሉን ታወቋል።
   መረጃው በማከል፣- የትራፊክ ፖሊስ አባል የሆነው ቢያርግልኝ ውቤ ከዚህ በፊትም በማይጨው ሞኾኒ መስመር ላይ እየሰራ እንደነበረና በሚፈፅመው አስነዋሪ ተግባር በሾፌሮች የተጠላ እንደነበረና በላዩ ላይ የተፈፀመው እርምጃም እንደሚገባው የአከባቢው ህዝብና ባለ አሽከርካሪቹ የመነጋገርያ አጀንዳ አድርገውት እንደሚገኙ መረጃው አክሎ አስረድቷል።