Wednesday, October 21, 2015

የአሕፈሮም ወረዳ ወጣቶች ተደራጅተው በህጋዊ መንገድ ተሰጥዋቸው ያለሙትን መሬት ያለ በቂ ምክንያት ከስራቸው ሰለታገዱ ለችግር መጋለጣቸው ተገለፀ።



   እነዚህ በማእከላዊ ዞን  በኣአሕፈሮም ወረዳ  ቀበሌ ዳጎስ  የሚገኙ  ወጣቶች በሕብረት ተደራጅተውና ሕጉ በሚፈቅደው መሰረት መሬት ተሰጥተዋቸው የተለያዩ ተክሎችን በመትከል ባመረቱት ምርት እራሳቸውንና ቤተሰቦቻቸውን  ሲያስተዳዱሩ ከቆዩ  በዉሃላ የወረዳው  አሰተዳዳሪዎች ግን  የምርት  ተካፋይ ባለመሆናቸው ያለ አግባብ ስልጣናቸውን ተገን በማድረግ ወጣቶቹ ስራቸውን እንዲያቆሙ  ሰለአደረጉዋቸዉ ከነቤተሰቦቻቸው ለችግር ስለተጋለጡ እግራቸው ወደ መራቸው ሰደት እየጠፉ መሆናቸዉን ተገለጠ።
   በመልካም አስተዳደር እጦት ምክንያት ለማህበራዊ ችግር የተጋለጡት ወጣቶች በማእከላይ ዞን ትግራይ ብቻ ሳይሆን  የስርኣቱ መሪዎች በፈጠሩት  ሱር የሰደደ የመልካም አስተዳደር  ችግር በመላው ኢትዮጵያ በመሆኑ ይህም ሃገሪትዋን ወደ ፍፁም ድህነት ያስገባ እንደሆነ የሃገራችን ሙሁራን በመግለጥ ላይ መሆናቸዉን ታውቀ።