Wednesday, October 21, 2015

በምእራብ አርማጭሆ ለጤና አገልግሎት የሚውል በቂ በጀት በገዥው ስርአት ባለመመደቡ የተነሳ ነዋሪዎቹ ከፍተኛ ችግር እየደረሰባቸው እንደሚገኝ ተገለፀ።



በአገራችን ከፍተኛ የግብርና ስራዎች ከሚከናወንባቻው አካባቢዎች የምእራብ አርማጭሆ ወረዳ ተጠቃሽ ሆኖ በወረዳው ውስጥ የሚገኙ የጤና ኬላዎች በተገቢ መጠን አገልግሎት የሚሰጡበት በጀት በገዢው ስርአት ስላልተመደበ በየአመቱ አጥጋቢ አገልግሎት መስጠት እንዳልቻሉ የወረዳው የጤና አመራሮችና ባለሞያዎች መስረት በማድረግ የተገኘው መረጃ አስረድቷል።
በምእራብ አርማጭሆ ወረዳ ያለው ነዋሪ ህዝብ 45 ሺ ነው በማለት ገዢውን ስርአት ያስቀመጠው አሃዝ በህዝቡ ቁጥር ብዛት  አመታዊ በጀት ቢመደብም እንኳ በተጨባጭ አሁን ያለውን የህዝቡ ብዛት ግን በእያንዳንዱ ቀበሌ በግማሽ እንደጨመረ የጠቀሱት ስማቸው እንዲገለፅ ያልፈለጉ የወረዳው  የጤና አማራሮችና ባለሞያዎች ወደ አካባቢው ከ2 እስከ 3 ሞቶ ሺ ለቀን ስራ ብለው የሚመጡ ጨምሮ የህክምና አገልግሎት የመስጠት ሃላፊነታቸው ለመወጣት እንዳስቸገራቸው ተናግረዋል።
በአካባቢው ባለው የወባ በሽታ ቡዙ ተንቀሳቃሽ ሰራተኞች እንደሚታመሙ የገለፁት እነዚህ ባለሞያዎች አብዛኛው መድሃኒት ለነዚህ ተንቀሳቃሽ ሰራተኞች ለማከም ከተጠቀሙለት የአከባቢው ነዋሪ ህዝብ የህክምና አገልግሎት ለማግኘት ወደ ጤና ኬላ በሚሄድበት ጊዜ መድሃኒት ከውጭ እንዲገዙ ስለማድረግ ወደ ጠብ እያመርዋቸው እንደሚገኙ ከገለፀ በኃላ በተጨማሪም በአካባቢው ለሚፈጠር ጊዜ ለማይሰጡ ተላላፊ በሽታዎች በአፋጣኝ መልስ ለመስጠት የሚመደብ በጀት ከህዝቡ ቁጥር ጋር ሲነፃፀር እዚህ ግባ የሚባልለት እንዳልሆነና ከአስር አመታት በፊት በነበረው የህዝቡ ቁጥር እንደሚበጀትላቸው ተጨባጭ ማስረጃ ያገኙበት አጋጣሚ እንዳለ ባለሞያዎቹ ጨምረው አስረድቷል።