በመረጃው መሰረት በደቡብ ክልል ቴፒ ከተማና
አካባቢው ልዩ ቦታ ሚልንየምና ሚካኤል በተባሉ አውራ ጎደናዎች መስከረም 29/ 2008 ዓ/ም ቅዳሜ ከለሊቱ 6 ስአት ካሳሁን የተባለው
ግለሰው የስርአቱ ተላላኪ በሆነው የፌደራል ፖሊስ ኣባል እንደገደለው ገልፆ የፌደራል ፖሊስ አባሉ ወደ ከተማዋ በቅርብ ጊዜ ተመድቦ
ሲሰራ እንደነበረ ታውቋል።
ሟዋቹ የፌደራል ፖሊስ የስራ ባልደረቦቹ ሆነ
ብለው እንደገደሉት እየተወራ እንኳ ቢሆንም አጋጥሞ ያለውን ሁኔታ ለማረጋጋት
የተሰማሩ የፌደራል ፖሊስ አባላት ግን የከተማዋ ወጣቶች እንደገደሉት ሲገልፁ በቴፒ ወረዳ ያለውን በህዝቡና በፌደራል
ፖሊስ አባላት መካከል ግጭት አንድ አመት ያስቆጠረ ሲሆን አሁን ያለውን ሁኔታ በአካባቢው ያሉት የፌደራል ፖሊስ አባላትና የፌደራል
ባለ ስልጣናት ያስደነገጣቸው ሲሆን በግጭቱ ምክንያት አምስት የፌደራል ፖሊስ አባላት በከተማዋ ወጣቶች ታግተው ወደ ማይታወቅ ቦታ
እንደተወሰዱ ለማወቅ ተችሏል።
በዚህም የተነሳ ወጣቶቹ አስቀድመው በፌደራል
ፖሊስ የታሰሩ ጓደኞቻቸው ሳይፈቱ አምስት የፌደራል ፖሊስ አባላት የሆኑት እንደማይለቅዋቸው አስታውቋል።
መረጃው ጨምሮ እንዳመለከተው በለፈው ሁለት
ሳምንታት በከተማዋ ሁለት የስርአቱ ካድሬዎችና የፖሊስ አባላት ሲገደሉ ፖሊሶቹ ደግሞ ለአንድ ንፁህ ዜጋ ገደለው እንደነበሩ ተገለፀ።