Friday, December 25, 2015

በአዲግራት ከተማ የፖሊስ አዛዥ ሆኖ ሲሰራ የቆየው ኮማንደር ፍታነገስ ስልጣኑን ተጠቅሞ የተለያየ የሙስና ተግባሮች ሲፈፅም ከቆየ በኃላ በአካባቢው ነዋሪ ህዝብ እንደተገመገመ ተገለፀ።



   በትግራይ ምስራቃዊ ዞን አዲግራት ከተማ የፖሊስ ኣዛዥ በመሆን ሲያገለግል የነበረ ኮማንደር ፍታነገስ የተባለ ፖሊስ፣ በነበረው ስልጣን ተጠቅሞ የማይገባውን ሃብት ለማካበት ጥሬ ገንዘብ እና ሌሎች ጉቦ የሰጡት ሕግና አሰራር የጣሰ እገዛ ሲያድርግላቸው፣ ግላዊ ጥቅሙ ሊያሟሉለት ላልቻሉ ተገልጋዮች ግን የማያስፈልግ ዉጣ ዉረድ በማስከተል ሲያስቸገራቸው እንደቆየ ተጎጂዎችን መሰረት በማድርግ የደረሰን መረጃ አስረድቷል።
   መረጃው በማስከተል የፖሊስ አዛዡ በተለያዩ ጥቅማ ጥቅሞች ትኩረት ያደረገ ሲፈፅማቸው የቆየ ኢ-ፍትሃዊ አሰራር ከህዝብ ትእዝብት የተሰወረ ባለመኖሩ፣ በዚህ ቅርብ ቀን በተካሄደ ስብሰባ የከተማው ነዋሪዎች ግልፅ የሆነ ሃሳብና መረጃ በማቅረብ ከስልጣኑ እንዲወርድ ማድረጋቸው ታውቋል።