Tuesday, December 29, 2015

በትግራይ ደቡባዊ ምስራቅ ዞን ሕንጣሎ ወጀራት ወረዳ የሚገኙ አስተዳዳሪዎች የህዝብ ገንዘብ ለግል ጥቅማቸው እያዋሉት እንደሚገኙ ተገለፀ።



በሕንጣሎ ወጀራት ኣዲ ወያኔ ቀበሌ ደንግላት ቀጠና የሚገኙ አስረዳዳሪዎች ከአስተዳደር የተላኩ መሬት ለሚልኩ ሰራተኞች የሚውል ገንዘብ ከአንድ ገበሬ 100 ብር እንድያዋጣ በማስገድድ ከ40 ሺ በላይ ወደ ፋይናንስ ገቢ ሳያድርጉ ወደ ግላዊ ጥቅማቸው እንዳዋሉት የገለፀው መረጃው ነዋሪዎቹ ላወጡት ገንዘብ የደረሰኝ ወረቀት እንዲሰጣቸው በሚጠይቁበት ግዜ ኣወንታዊ መልስ ሊያገኙ እንዳልቻሉ ለማውቅ ተችለዋል።
    መረጃው ጨምሮ እንዳስረዳው፣ ለመሬት ሽግሽግ የሚዉል ነፍስ ወከፍ ገብሬ 5 ብር እንዲዋጣ በህዝብ የታመነለት ቢሆንም፣ አስተዳዳሪዎቹ ግን ስልጣናቸው ተጠቅመው ህዝብ ያላመነበት 100  ብር እንዲከፍል ከህግ ዉጭ ማስገደዳቸው ሳይበቃ፣ መሬት ለሚሰጡ ሰዎች ቢሆንም የቀን ዉል አበል በመንግስት እየተሰጣቸው እያለ፣  በተጨማሪ ከህዝብ በስማቸው 100 ብር በመዋጣት አስተዳዳሪዎችና የመሬት ኣካፋፋዮች ተባብረው ለነዋሪው ህዝብ ገንዘቡን በመዝረፍ ስራ ተሰማርተው እንደሚገኙ ለማቀቅ ተችለዋል።