በዚህ ሳምንት የሀገራችን
ወቅታዊ ሁኔታ አስመልክቶ የአውሮፓ ህብረት ከኢትዮጵያ መንግስት ባካሄደው ውይይት፣ በኦሮሚያ ክልል ውስጥ
በኢህአዴግ ስርአትና በተቃዋሚ ህዝብ መካከል በተነሳው
ግጭት የስርአቱ ታጣቂ ሃይሎች በሲቪል ህብረተሰብ ላይ ያወረዱት ሰብአነዊት የጎደለው
አረመኔዊ የመግደል እርምጃ ተከትሎ ግጭቱ፣ በሰለማዊ መንገድ እንዲፈታና ሁለንተናዊ ውይይት የሚደረግ
ለተቃወመው ህዝብ፣ በሃይል ጨቁኖ በመያዝ ሳይሆን ህግ የሚከበርበትን ዘላቂ መፍትሄ በሚያመጣ መንገድ መካሄድ እንዳለበት ተብሎ የተላከው ቡዱን ለኢትዮጵያ መንግስት ጥያቄ እንዳቀረበ ለማወቅ ተችሏል።
የአውሮፓ የህብረት ተወካዮች ጨምረው በአገራችን
መረጋጋትና ሰላም እንዲኖር በስልጣን ላይ ያለው ገዥው የኢህአዴግ ስርአት፣
መደረግ የሚገባውን ሰላማዊ መፍትሄና ኢትዮጵያውያን ሰደተኞች ለመቀነስ ዘላቂ የሆነ መፍትሄ እንዲመጣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ
ከስርአቱ ባለ ስልጣኖች ጋር ተገናኝተው ሃሳባቸውን እንዳካፈልዋቸው የሚታውቅ ሆኖ፣ የገዤ ስርኣት ባለ ስልጣናት ግን የስልጣናቸው ህልዉና በኣደጋ ላይ እንደሚወድቅ በመፍራት በኦሮሞ
ተወላጆች የመግደልና የማሰር እርምጃውን አጠናክሮ እየቀጠለ መሆኑን የተገኘው መረጃ ኣስረድተዋል።