በስልጣን
ያለው ገዥው የኢህአዴግ ስርአት በቢልዮን የሚቆጠር ገንዘብ ወጪ ተደርጎላቸው በመሰራት ላይ ናቸው፡ የሚላቸው ፕሮጀክቶች ከፈተኛ ሙስና ተግባር የሚፈጸሙባቸው ተብለው በሞያተኞች እንደሚጠቀሱ ይህ የሙስና ተግባር ሊጣራ ከሆነ ደግሞ የሚመለከታቸው አካላት የሚባሉት የጸረ ሙስናና የሰነ-ምግባር ኮሚሽን
ትኩረት አድርገው እንዲሰሩ ይገባቸዋል የሚል ማሳስብያ በዚህ ሳምንት በንግድ የሚተዳደሩት ዜጎች ባካሄዱት ስብሰባ ላይ እንዳቀረቡ
ለማወቅ ተቻለ።
በስብሰባው
ወስጥ በሞያተኛታት የተዘጋጀው ጽሑፍ እንደሚያስረዳው የጸረ ሙስና ኮሚሽኑ
ችግሮች ከተፈጠሩ በኋላ መንቀሳቀስ ሳይሆን የሚገባው የህዝብና የሃገር ሃብት ከመዘረፉ በፊት ለመከላከል የሚያስችል የሰነድ
ዝግጅት መከታተል ስራው እንደሆነ ሊያውቀው ይገባል ብለው፡ በተለይ
ደግሞ በትላላቅ ፕሮጀክቶች በተጨማሪም በመሬት አስተዳደር በግብር በፍትሕ አሰጣጥ በአጠቃላይ በሙስና ምክንያት 40% የሚሆነው የመልካም አስተዳደር ጠንቅ መሆኑን በጥናት የተደገፈ ሪፖርት ከተገለጸ
በኋላ በላይኞቹ መሪዎችም በተግባር የተመሰረተ ክትትል በማድረግ ጥፋት ላይ በሚፈጽሙ አስተማሪ የሆነ እርምጃ መወሰድ እንደሚገባ
ተገለጸ።
No comments:
Post a Comment