በየጊዜው በፍትህ ሚኒስተር እየረቀቁ የሚወጡ ህገ-ደምብ ተብለው ሊጸድቁ ወደ ምክር ቤት የሚቀርቡት ህጎች ከነብዙ ችግሮቻቸው ሊጸድቁ ከተደረጉ
በኋላ በተግባር ሲታይ ግን ክፍተቱ ጎልቶ ስለ ሚታይ በአፈጻጸም ላይ
ያልተሟላ ስራ እንደሚስራና እንቅፋት የበዛበት ችግር እንዲፈጠር ጠንቅ እየሆኑ ናቸው በማለት፡ የፍትህ ምክር ቤቱ በዚህ ሳምንት ባካሄደው ሰብሰባ ላይ መገምገሙን ተገለጸ።
ህገ መንግሰቱ
መሰረት ያደረጉ ተብለው የረቀቁ ደንቦችና መመሪያዎች ህግ ሆነው በፖርላማ ከመጽደቃቸው በፊት ፍትህ ሚኒስተሩ እንዲመለከታቸው ቢደረግም
እንኳ ፍትህ ሚኒስተሩ ግን እያንዳንዱን አንቀጽ በመፈተሸ ላይ ችግር ሰለ አለው፡ በቅርብ
ጊዜ የውጭ ሰራ የመስራት አዋጅ እርምጃ ተብሎ የውጣ ህግ ብቻ ሲታይ ከሃያ አንቀጽ በላይ ችግር ያለው ሆኖ ሰለተገኘ፡ ማሻሻያ
ተደርጎለት እንዲጸድቅ እንደተደረገ መረጃው ጨምሮ አሰገንዝቧል።
መረጃው
በመጨረሻ፡ የወጡት ህጎች በሚገባ ታይተዋል
እየተባሉ ቢቀርቡም እንኳ በሕግ አርቃቂዎችና ለረቀቀው ህግ የሚፈትሹ
የፍትህ አካላት የአቅም ችግር ሰለ አላቸው እስከ አሁን ደረስ የተጣራና
የተሰተካከለ ህግ ሊያወጡ ባለመቻላቸው የተነሳ በሰብአዊና በዴሞክራሲያዊ መብት ጥሰት ላይ የራሳቸው ክፍተት ፈጣሪዎች ሆነው ሰለተገኙ፡ የሚወጡት ህጎች ገና አመት ሳይሰራባቸው ዳግም መሻሻል ሊደረግላቸው በመገደድ
ላይ መሆናቸውን ለማውቅ ተችሏል፡
No comments:
Post a Comment