አለም አቀፍ የሃይል ኢነርጂ ምክር ቤት ባወጣው ሪፖርት መሰረት ኢትዮጵያ
በአሁኑ ጊዜ ከኤሌክትሪክ ሃይል ሽያጭ ገቢ ለማግኘት በሚል ከጎሮቤት አገሮች የምታካሂዳቸው ስምምነቶች ለፖለቲካዊ ፍጆታ እያዋለችው
እንዳለች ከገለፀ በኋላ በአሁኑ ጊዜ አገሪትዋ የምትጠቀምባቸው ያለች 2፣368 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ሃይል ሆኖ መቸ ተሰርቶ እንደሚጨረስ
ባልተገደበበት ጊዜ ታስቦ የኤሌክትሪክ ሃይል የማመንጨት አቅሙ ከ10 ሺ ሜጋ ዋት በላይ ነው በማለት ከኬኒያ፤ ጅቡቲና ሱዳን የኤሌክትሪክ
ሃይል ማመንጫ ስምምነት በማድረግ እንዲሁም ከሩዋንዳ፤ ታንዛኒያ፤ ደቡብ ሱዳንና ብሩንዲ በድርድር ላይ እንዳሉ ጨምሮ አስታውቋል።
የኤሌክትሪክ ሃይል ሽያጭ ቀደም ሲልም ከጎሮቤት አገሮች በርካሽ ዋጋ
እንደጀመረችው የገለፀው መረጃው በአሁኑ ጊዜ በርከት ያሉት አገሮች በማድረግ ያለችው የሽያጭ ስምምነቶች ዋጋው በጣም የወረደና የአለም
ኤሌክትሪክ ሃይል ሽያጭ ዋጋ ያላገናዘበ በመሆኑ የዋጋው ድርድር ለኢኮኖሚ ጥቅም ታስቦ ሳይሆን ለፖለቲካዊ ፍጆታ ተብሎ ነው በማለት
ባለፈው ሳምንት አለም አቀፉ የኢነርጂ ሃይል ምክር ቤት ለውሃና መስኖ ሚኒስተር ባለስልጣን ደብዳቤ እንደላከ ለማወቅ ተችላል።
መረጃው በመጨረሻ አገራችን ኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ ካለፉት አመታት በከፋ
መልኩ በኤሌክትሪክ ሃይል አቅርቦት ችግር ምክንያት ህዝቡ በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ኑሮው ላይ ለመመራት ሳይረጋጋ ጥያቄዎቹ ሳይመለሱለት ለጎሮቤት አገሮች ለመሸጥ ስምምነቶችና ድርድሮች ማካሄድ በህዝቡ ላይ ማላገጥ ነው ሲሉ የተለያዩ
ወገኖች በመግለፅ ላይ እንደሚገኙ ይታወቃል።
No comments:
Post a Comment