መረጃው እንደገለፀው በአዲስ አበባና ዙሪያዋ
የሚገኙ የኦሮሚያ ልዩ ዞን ከተሞች በመሰረተ ልማት ማስተሳሰር በሚል የወጣውን አዋጅ ተከትሎ የተነሳ ተቃውሞ ወደ መላው የኦሮሚያ
ክልል ከተሞችና የገጠር አካባቢዎች በመስፋፋት ታህሳስ 25 2008ዓ/ም ትም ቀጥሎ እንደዋለ ለማወቅ ተችሏል።
በዚህ መሰረት ደግሞ በምስራቅ ሃረርጌ የሚገኝ የአዳማ ዩንቨስቲ በተጠቀሰው
እለት ቀጥሎ የዋለውን ተቃውሞ ለማገት በርከት ያሉትን የፖሊስ አባላት ወደ ዩንቨርስቲው ቅጥር ግቢ ዘልቀው በመግባት በቶክስና በሚያነባ
ጭስ ሊበትኗቸው ሞክረው ሊሆንላቸው አልቻለም ሲል አንድ ስሙን ሊገልፅ ያልፈለገው የዩንቨርስቲው ተማሪ ገልጿል።
ተማሪው በማከል እንዳስረዳው በዩንቨርስቲው የሚማሩ ተማሪዎች የኦሮሚያ
ተወላጆች ተቃውሞ እንዳያስነሱ በፀጥታ አካላት እየተለዩ ወደ ማይታወቀው የዩንቨርስቲው ቦታ እየሰበሰብዋቸው እንደሚገኙ ሲገልፅ በተቃውሞው
ተሳትፎዋል ያሉዋቸውን ከ150 በላይ ተማሪዎች ደግሞ ታስረው እንደሚገኙ
አስታውቋል።
በመጨረሻ በዚህ ጊዜ በዩንቨርስቲው ከፍተኛ ውጥረት ነግሶ እንደሚገኝና
በዩንቨርስቲው ዙሪያ በርከት ያሉትን የፀጥታ ሃይሎች ተከማችተው እንዳሉ በመግለፅ ይህ ደግሞ ዩንቨርስቲ ሳይሆን ወታደራዊ ማሰልጠና
ማእከል መስሎ እንደሚገኝ መረጃው ጨምሮ አስረድቷል።