Monday, January 11, 2016

በዲላ ዩኒቨርስቲ ውስጥ በተከስተ የቦንብ አደጋ ተከትሎ መምህራንና ተማሪዎች ስራቸውን ያቆሙ መሆኑ ተገለፀ።



    ከታህሳስ 26/2008 ዓ/ም ጀምሮ በዲላ ዩኒቨርስቲ የሚማሩ ተማሪዎች ትምህርታቸውን እንዳቆሙ የገለፀው መረጃው፣ እነዚህ ተማሪዎች የ1 አመት ፈተና ለመውሰድ ሁለት ሳምንት ብቻ ሲቀራቸው መማራቸውን አቋርጠው ወደ ትውልድ ቦታቸው እንደተመለሱና ዩኒቨርስቲው የመማርና የማሰተማር ሂደቱ   እንዳቆመ ለማውቅ ተችሏል።
   በተፈጠረው ችግር ተከትሎ፣ በዲላ ከተማ ውስጥ ከመጠን በላይ የሆነ የትራንስፖርት ችግር እንደተከሰተና በመምህራንና ተማሪዎች ደግሞ ብዙ መንገለታታት እንዳጋጠማቸው እየገለፀው መረጃው፣  ከአሁን በፊት ከዲላ ወደ አዋሳ 40 ብር የነበረው የትራንስፖት ዋጋ  በአሁን ወቅት  እስከ 320 ብር የደረሰ መሆኑንና ይህ ደግሞ  ሆን ተብሎ ካለው ሁኔታ ጋር ተሳስሮ በገዢው ሰርአት የተደረገ ተንኮል መሆኑ ያገኘነው መረጃ አስረድቷዋል።