Friday, January 22, 2016

በልማት ስም ለኢትዮጵያ የሚሰጥ እርዳታ በየአመቱ እየጨመረ በመሄድ ላይ ቢሆንም ገንዘቡ ግን ባልታለመለት ስራ እየዋለ መሆኑ ለማወቅ ተችለዋል።



    በመረጃ መሰረት፣ አለማቀፍ የኢኮኖሚ ልማት አስተባባሪ ማሕበር ያደረገው ደገፍ፣ ዩናይትድ ስቴትስ፤ እንግሊዝ፤ እንዲሁም የልማት ኮሚቴ መተጋገዝ አባል አገሮች 137.2 ቢልዮን ዶላር የተመዘገበ የልማት ደገፍ፣ አገራችን ኢትዮጵያ የድጋፉን ተቀባይ በመሆን በአንደኛ ደረጃ እንደተጠቀሰች ከገለፀ በኃላ፣ ይህ ደግሞ በ2014 የአዉሮፓን አቆጣጠር የተመዘገበ ሆኖ ከ 2013 ዓ.ም በሁለት ሚልዮን ዶላር ያደገ ሆኖ እንደተገኘ ተገለፀ።
     በአለማችን በድርቅ እና በረሃብ የምትታወቅ አገራችን ጥግተኛና ተረጂ  ከሆኑ አገሮች አንድዋ ሆና በአጠቃላይ በ2014 ዓ.ም ከማሕበረሰብ አለም የተሰጣት የልማት ደገፍ 3.6 ቢልዮን ዶላር የነበረ ሲሆን የኢኮኖሚ አስተባባሪ እና የልማት ማሕበር ኢፋ ባደረገው መረጃ መሰረት ደግሞ ለድሃ አገሮች የተሰጠ የልማት ደገፍ  በሚመለከት በመካከለኛ ለኢትዮጵያ  የታወቀ የልማት ደገፍ በመስጠት የአለም ባንክ አንደኛ ደረጃ ስይዝ ዩናይትድ ስቴትስ እንግሊዝ የአፍሪካ ፈንድ ልማትና የአዉሮፓ ህብረት በቀደም ተከተል እንዲጠቀሱ ችለዋል።
  ኢትዮጵያ ከአለም ማሕበረሰብ የተቀበለቺው የተመዘገበ ደገፍ ለተለያየ ልማታዊ ስራዎች እንዲዉል የሚል ሲሆን ዋናኛው አላማቸው ግን ለስቪክ ማሕበራት በማሕበራዊ ጉዳዮች ለሚዉሉ የወሃ አቅርቦት ለትራንስፖርት ለእርሻ ለደን ለአሳ ልማት ሃፍት ለኢንዱስትሪና ለመአድን ክፍል  እንዲዉል ተብሎ የሚሰጥ ደገፍ ቢሆንም የኢህአዴግ ስርአት ግን የዜጎቻችን  ሰበአዊ መብት በማፈን ስራ ላይ ስለሚያዉለው የተለያዩ ወገኖች እና መንግስት እየተወቀሱ እንደሚገኙ መረጃው ጨምሮ አስረድተዋል።


                        

No comments:

Post a Comment