ባገኘነው መረጃ መሰረት የምግብ ቅድመ ማስጠንቀቅያ ስርአት የተባለ ድርጅት፣ እንዳስታወቀው የአለም ለጋሾች ለድርቁ ለመከላከል
እንዲሰጡ ከተጠየቁት እርዳታ፣ የተሰጠ አናሳ በመሆኑ በአገራችን አጋጥሞ ያለው ድርቅ ወደ ከፋ ረሃብ ይሸጋገራል ሲል የምግብ እጥረት ቅድመ ዝግጅት ድርጅት
እንዳስጠነቀቀ ታዉቀዋል።
በአገራችን ተከስቶ ባለው ድርቅ ለምግብ እጥረት የተጋለጠ ህዝብ በፊት ከተሰጠው
ግምት በላይ ሊሆን እንደሚችል አለም አቀፍ ድርጅቶች እያስታወቁ መሆናችው
የገለፀው መረጃው፣ በስራው የተሰማሩ ድርቶችእና ማሕበራት እንደሚሉት በ2016 የአዉሮፓ አቆጣጠር የምግብ እርዳታ የሚፈልግ የህዝብ
ቁጥር ከግዜ ወደ ግዜ ይጨምራል ካሉ በኃላ የምግብ እጥረት ቅድመ ማስጠንቀቅያ የተባለ ተቛም ደግሞ የአለም ለጋሽ አገሮች ድርቅ
ለመከላከል ተብሎ የተጠየቁት እርዳታ በጣም እናሳ በመሆኑ የምግብ እጥረትና የረሃብ አደጋ በጣም አስጊ ነው በማለት ለአለም ማሕበረሰብ
አነጋጋሪ አርእስት ሆኖ እየቀጠለ መሆኑ ለማወቅ ተችለዋል።
No comments:
Post a Comment